ጥፍር ቀለሞ ስለ እርሶ ምን ይላል

ጥፍር ቀለሞ ስለ እርሶ ምን ይላል

ፈዛዛ ሮዝ

ፈዛዛ ሮዝ ቀለም ለየትኛውም ቢሮ እንዲሁም ለየትኛውም ወቀት እና ዝግጅት የሚሆን ቀለም ሲሆን ይህ ቀለም ሙያዊነቶን ያሳያል።

ቀይ

ቀይ ቀለም በራስሽ እንደምትተማመኚና ተለይቶ ለመታየት ዝግጁ እንደሆንሽ ያሳያል በፀሃያማ ወቀት ይህ ቀልም ይዘወተራል ምንም ደማቅ ቢሆን ቀይ ቀለም ሁሌም ክላሲክ ነው።

ነጭ ቀለም

ይህ ቀለም ለተለያዩ አማራጮች ክፍት እንደሆነ ያሳያል ለሁሉም ወቅቶች የሚሆን ቀለም ሲሆን ግን እንደሌሎች ቀለሞች አይቆይም።

ውሃ ቀለም

ይህ ቀለም ስለ ገፅታዎ እንደሚያስብ ነገር ግን ጊዜ እንደሌሎት ያሳያል።

ጥበባዊ ንድፍ

ይህ ቀለም ምንም ነገር መሞከር እንደማትፈሪ እና ግለሰባዊ እንደሆንሽ ያሳያል ለገፅታሽም ጊዜ እንደምሰጪ ያሳያል።

ደማቅ ቀለሞች

ሰማያዊ፣አረንጏዴ እና ወይንጠጅ እነዚ ቀለሞች እንደ ፈዛዛ ሮዝና ቀይ ሁሌ የሚደረጉ ባይሆንም ከአለባባሶት ጋር በማስማማት መጠቀም ይቻላል።

ኒዮን ቀለም

እነዚ ቀለሞች ለስራ ቦታ አይሆኑም ለመዝናናት አልያም ዝግጅቶች ላይ ቢደረጉ ይመረጣል ።

ጥቁር

ጥቁር ልብስ ስልጣንን እና ሀይልን እንደሚያሳይ ሁሉ ጥቁር ጥፍር ቀለምም ይህንኑ ያንፀባርቃል።

Leave a Reply