ጅንስ ከመግዛቶ በፊት ማወቅ ያለቦት ነገሮች

ጅንስ ከመግዛቶ በፊት ማወቅ ያለቦት ነገሮች

ትክክለኛው ጅንስ መግዛት ለወንድንም ለሴትም አስቸጋሪ ነው ዛሬ ግን ወንዶች ላይ እናተኩራለን በጅንስ ግብይት ውስጥ ብዙ ሊበላሹ የሚችሉ ነገሮች አሉ ግን የሚከተሉትን ምክሮች ተግባራዊ ካደረጉ የተሳካ ግብይት ይሆንሎታል፡፡

1.ልክ

ይህ የሚመለከተው ስለ ሱሪው ስፋት ነው ፡፡ የተለያዩ አይነት የሱሪ ስፋት አሉ ግን በአጠቃላይ የወንድ ሱሪ ከስፋት አንጻር በ3 ይከፈላል ቡት ቁርጥ፣ቀጥ ያለ እና ስኪኒ በመባል ይከፈላሉ፡፡

i. ቡት ቁርጥ፡- ከጉልበት በታች እየሰፋ የሚሄድ አይነት ሱሪ ሲሆን በጣም ሊያሶግዱት ይገባል፡፡

ii. ቀጥ ያለ፡- ይህ የሱሪ አይነት ለየትኛውም ወንድ የሚሆን ነው ከጉልበት በታች ትንሽ የሚጠብ ሲሆን እንደ ስኪኒ ከቆዳችን ጋር አይጣበቅም ትንሽ ከስኪኒ ለቀቅ ያለ ነው፡፡

iii. ስኪኒ ጅንስ፡- ይህ ደግሞ ካሉት ሁሉ ጠባብ ነው፡፡ ከጉልበት በታች እያጠበበ የሚሄድ ወደ ቁርጭምጭሚት ጋር ሲደርስ ጥብቅ የሚል ነው፡፡

2.ከፍታ

ጅንስ ሲገዙ ከወገቦ በጣም ዝቅ ያላለ መካከል ላይ ቢገዙ ይመረጣል፡፡

Leave a Reply